Newsletter Help
Change language Amharic (አማርኛ)

እንዴት አባል መሆን ይቻላል

Become a KPR member, and enjoy cheaper prices immediately. Register here.

Delivery to 24 countries is now much cheaper. Click here to learn about new shipping fees to your country.

የአባልነት ምዝገባ ቅጽ

የKPR አባል መሆን ፈልጋለው

ስለአባልነት መረጃ

ከ2007 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ጀምሮ የስሎቫክ ቋንቋ ለማይችሉ ሁሉ የKPR አባሎች እንዲሆኑ ተፈቅዶአል።
በ2000 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ክለባችንን በስሎቫክ ቋንቋ ጀምረን ነበር። ከዚያኔ ጀምሮ ብዙ አባሎች ከስሎቫኪያና ቼክ ገብተዋል።
አሁን ግን ማንም ሁኑ ምንም ቋንቋ አውሩ የKPR አባል በመዎን የአባልነት ጥቅምን ማግኘት ይችላሉ።
በአለም ዙሪያ ያሉ ማንኛውንም የአትክልት ወዳጆችን እንጋብዛለን። አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ምንም ቢሆን ግን አንድ ትንሽ ችግር አለ። ቋንቋውን ካልቻሉ ቦታኒክስ የተሰኘውን የክበባችንን ህትመት ማንበብ ላይችሉ ይችላሉ። በሌላ አስተያየት ግን ለምን የራስዎን የቦታኒክስ ህትመት አይጀምሩም? በአካባቢዎ ከሚገኙ ሌሎች አትክልተኞችና አትክልት ወዳጆች ጋር ተባብራቹ በራሳችሁ ቋንቋ ስለአትክልቶች አስደናቂ አስደሳች እንዲሁም ኣስተማሪ የሆኑ ጽሁፎችን ማተም ይችላሉ።
ለግልዎ የልብ ሙላት ምንም ገድብ የለም!
በዚያም ላይ በስሎቫኪያ የሚሰራው የአትክልትና ትሮፒካል ሁኔታ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ በሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ተክሎች ትክክል ላይሆን ይችላል። ስለዚህም በየራስዎ ቋንቋና ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ቦታኒክስ መጻፍ ይህንንም ይረዳል።

የKPR ስሎቫኪያ አባልነት

ለምን የKPR አባል መሆን አለብዎት?

1. የKPR አባሎችን ትዕዛዞቻቸውን በቅናሽ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ። ከታች ያሉትን ምሳሌዎች ይመልከቱ። (ለትዕዛዞች አነስተኛ የሆነ ልክ የለም)

ዋጋ: ለKPR አባሎች ዋጋ: አባል ላልሆኑ % - ቅናሽ
0,50 € 0,70 € 29%
0,70 € 0,90 € 22%
1,00 € 1,50 € 33%
3 € 4 € 25%

2. እያንዳንዱ አባል በየአመቱ 5 ነጻ የዘር ሳምፕሎች ከKPR የዘሮችና ተክሎች ባንክ መውሰድ ይችላል። (ከፓልምስ፣ ሳይዳድስ እና የተወሰኑ የተመረጡ ዝርያዎች ዘር በስተቀር) ከዚህም በተጨማሪ አባሎች ለተወሰኑ ዝርያዎች የ50% ቅናሽ ድረስ ይሰጣቸዋል። (ለአንድ ሳምፕል ደንበኛው ዋጋ 1 ዩሮ ቢሆንም ለአባሎች 0.50 ዩሮ ብቻ ይሆናል ማለት ነው)

3. የKPR አባሎች ትዕዛዞች ከአባል ያልሆኑ ትዕዛዞች በፊት ቅድምያ ይሰጣቸዋል።

4. ኣመቱን ሙሉ ስለ አትክልቶች በተመለከተ በ11 ቋንቋዎች ነጻ የምክር አገልግሎት

የክፍት አካውንት አገልግሎትን መጠቀም ይችላሉ።

ክፍት አካውንት - ስለክፍት አካውንት የበለጠ መረጃ
ክፍት አካውንት ከKPR ለመግዛት በጣም አመቺው መንገድ ነው። ምንም ከማዘዝዎ በፊት ገንዘብ ይልኩልንና በክፍት አካውንትዎ ውስጥ ይቀመጥልዎታል። ከዚያም ምንም ነገር ማዘዝ ከፈለጉ ከአካውንትዎ ላይ ይከፈላል። ይህም ማለት ትዕዛዝ ሲያስገቡ ገንዘቡ እስከሚመጣ በመጠበቅ ሰዓት አናቃጥልም ማለት ነው። ትዕዝዝዎም ወዲያውኑ ይስተናገድልዎታል እናም ይላክልዎታል። በፈለጉት ጊዜ ወደ ክፍት አካውንትዎ ገንዘብን መጨመር ይችላሉ።
ገንዘብ ወደ ክፍት አካዎንትዎ መጨመር በሚፈልጉበት ጊዜ ይክፍያዎን ምክንያት ለማወቅ እንዲያመቸን የግል ቁጥርዎን አብረው ይጻፉልን። ከዚያም ገንዘቡ እንደደረሰን ወደ አካውንትዎ እንጨምርልዎታለን። ወደ ክፍት አካውንትዎ መጨመር ለምትችሉት ገንዘብ ገደብ የለውም። ገንዘቡ ወደ ክፍት አካውንትዎ እንደገባ የአካውንትዎን ባላንስ መጠቀም ይችላሉ።
ክፍት አካውንትዎን ተጠቅመው ለትዕዛዝዎ መክፈል ከፈለጉ እንደሚከተለው አይነት መልዕክት ለከው ያሳውቁን: “ ሰትዕዛዜ የምከፍለው የክፍት አካውንቴን ቁጥር XXXXXXX በመጠቀም ነው። ” ትዕዛዝው እንዳለቀ ገንዘቡ ከአካውንትዎ ተከፍሎ እቃውም ወዲያውኑ ይላክልዎታል።
በፈለጉት ጊዜ ከክፍት አካውንትዎ ገንዘቡን መልሰው መውሰድ ይችላሉ። ነገር ግን የተወሰነ ገንዘብ ለመመለሻው እንደሚያስከፍላቹ ልብ ይበሉ። በPayPal በመጠቀም ገንዘቡ ከተመለሰልዎት ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም። እንዲሁም በMoneyBookers.com ለመመለስ ክፍያው 0.50 ዩሮ ብቻ ነው። በስሎቫኪያ ወይም በቼክ በሚገኙ ባንኮች የገንዘብ ዝውውር በማድረግ ለመመለስ ምንም ክፍያ አያስፈልግዎትም። ለሌሎች ሀገሮች ወይም የክፍያ መንገዶች ግን ስለሚያስፈልጉ ክፍያዎች እኛን ይገናኙን። ትዕዛዙን በሰጡን በ60 ቀናት ውስጥ ገንዘብዎን እንመልስልዎታለን።
መረጃ: ክፍት አካውንት መጠቀም በየጊዜው ትዕዛዝ ሲያደርጉና ክፍያ ሲፈጽሙ የሚያወጡትን ወጪ ያስቀርልዎታል። ማድረግ የሚጠበቅብዎ ብቻ ክፍያ በሚፈጽሙ ቁጥር ገንዘቡን ከዚያ አካውንት ማዛወር ብቻ ነው።
ጥያቄ አልዎት?

6. በ2019 ዓ.ም እ.ኤ.አ ያዘዙት ትዕዛዝ ከ80 ዩሮ በላይ ከሆነ እስከ 10 ዩሮ ድረስ የሚሆን የዘር ትዕዛዝ በነጻ ይሰጥዎታል።

7. አመታዊ ሎተሪ ከ50 ፣30፣ 15 ዩሮ የሚሆን ከነጻ የማጓጓዣ ወጪ ጋር!

...እናም ስለብዙ ሌላ ጥቅማ ጥቅሞች እንነግርዎታለን።

የአባልነት ሁኔታዎች

1. የአባልነት መመዝገቢያ ቅጽ መሙላት ይኖርብዎታል። እንዲሁም የ10 ዩሮ የአመታዊ የመመዝገቢያ ክፍያ ከተመዘገቡበት አመት May 31 በፊት መክፈል ይኖርብዎታል። ይህ የሚከፍሉት የመመዝገቢያ ክፍያ የKPRን አለም አቀፋዊ አገልግሎቶች ለማስፋፋት ይጠቅማል።

2019 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. አመታዊ የአባልነት ክፍያ

አባልነትዎ ከ1.10.2018 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. እስከ 31.12.2019) ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ድረስ የተጠበቀ ይሆናል።

አመታዊ ምዝገባ የመጀመሪያ አመት ለሚቀጥለው አመት ማሳደስ
10 Euro 5 Euro

2. በአመት ቢያንስ 2 ትዕዛዞችን ለክበቡ ማስገባት ይጠበቅብዎታል። ለትዕዛዝዎቹ አነስተኛ የተባለ ገደብ የለም።

3. ከፈለጉም በግልዎ አስተዋጽዎ ለKPR ድጋፍ የሚሆን ክፍያ መፈጸም ይችላሉ። ይህም ገንዘብ በአለም ዙሪያ የKPRን ስር ለማስፋፋት ይጠቅማል።

የKPR አባል ለመሆን ይፈልጋሉ? በጣም ቀላል ነው! አሁኑኑ ይግቡ። ይህንን የምዝገባ ቅጽ ብቻ ይሙሉ።

የአባልነት ምዝገባ ቅጽ

የKPR አባል መሆን ፈልጋለው


ይንን እቃ ወደ ግዢ ሳጥንዎ ከትተውታል።